በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጠ።

43

ኬሚሴ፡ ሐምሌ 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክር ቤት 5ኛ ዙር 1ኛ መደበኛ አስቸኳይ ጉባኤ አካሂዷል።

ምክር ቤቱ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የምክር ቤቱን ዋና አፈጉባኤ እንዲሁም የዞኑን ዋና አስተዳዳሪ እና ምክትል ዋና አስተዳዳሪን ጨምሮ የተለያዩ ሹመቶችንም ሰጥቷል።

በዚህም መሰረት ፦

1.ወይዘሮ ፋጡማ ሞላ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ

2. አቶ አሕመድ አሊ አባፍሮ – የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ዋና አሥተዳዳሪ

3. አቶ አብዱ ጀማል – የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ምክትል ዋና አሥተዳዳሪ እና የሰላም እና ደህንነት መምሪያ ኅላፊ

4. አቶ ሰይድ መሐመድ – የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የከተሞች እና መሰረተ ልማት መምሪያ ኅላፊ

5. ኢንጅነር ሀሊማ ኡመር -የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የውኃ እና ኢነርጂ መምሪያ ኅላፊ

6. አቶ ኢብራሂም አልዬ – የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የሥራና ስልጠና መምሪያ ኅላፊ

7. አቶ ዘሪሁን በቀለ – የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የመሬት መምሪያ ኅላፊ

8. አቶ እንድሪስ አሕመድ – የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የትምህርት መምሪያ ኅላፊ

9. አቶ አሕመድ ጅብሪል – የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የቆላ እና መስኖ መምሪያ ኅላፊ

10. ወይዘሮ ሀሊማ ይማም – የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያ ኅላፊ

11. አቶ እንድሪስ አሊ – የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የፍትህ መምሪያ ኅላፊ

12. አቶ ሲራጅ ጀማል – የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የማዕድን ሀብት ልማት መምሪያ ኅላፊ

13. አቶ ሰለሞን ይትባረክ – የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ኅላፊ

14. አቶ መሐመድ ሲራጅ – የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የመንገድ መምሪያ ኅላፊ ኾነው ተሹመዋል።

ዘጋቢ ፦ ተመስገን አሰፋ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“እኛ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ተፋላሚ ኀይሎች ሰላም ፈጥረው ሕዝቡ እፎይታ እንዲያገኝ እንሠራለን” የጠለምት ወረዳ የሰላም ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች
Next articleበክልሉ የተፈጠረው ግጭት በውይይት እንዲፈታ የበኩላቸውን እንደሚወጡ የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት ሠራተኞች ተናገሩ፡፡