የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በልዩ ልዩ የትምህርት አይነቶች ያሰለጠናቸውን 885 ተማሪዎች አስመረቀ።

32

ደብረ ብርሃን፡ ሐምሌ 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ7 ልዩ ልዩ የትምህርት ዘርፎች ለ26ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 885 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል። ከተመረቁት ውስጥ 449 ወንዶች ሲኾኑ 436 ሴቶች ናቸው።

የኮሌጁ ዲን ባሻዬ በየነ በ1989 ዓ.ም የተመሰረተው የደብረብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በርካታ ተማሪዎችን በማስመረቅ ከሥራ ጋር እንዲተሳሰሩ አደርጓል ብለዋል።

ኮሌጁ ከምስረታው ጀምሮ 500 የሚኾኑ ዝቅተኛ የገቢ አቅም ያላቸውን ተማሪዎች ተቀብሎ በነጻ ማስተማሩን ተናግረዋል፡፡

የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ በእውቀት፣ ክህሎት እንዲሁም በፈጠራ አቅም ያደገ ትውልድ በማፍራት ጉልህ ሀገራዊ አበርክቶ እንዳለው አቶ ባሻዬ ተናግረዋል።

በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የደብረብርሃን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት ኮሌጁ በጥራት እና በብቃት ተማሪዎችን እያሰለጠነ ስለመኾኑ ተናግረዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሀገራዊ የመጠጥ ውኃ ሽፋን 69 ነጥብ 5 በመቶ መድረሱን የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ።
Next article“እኛ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ተፋላሚ ኀይሎች ሰላም ፈጥረው ሕዝቡ እፎይታ እንዲያገኝ እንሠራለን” የጠለምት ወረዳ የሰላም ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች