ሀገራዊ የመጠጥ ውኃ ሽፋን 69 ነጥብ 5 በመቶ መድረሱን የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ።

25

አዲስ አበባ፡ ሐምሌ 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በበጀት ዓመቱ የመጠጥ ውኃ ሽፋን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር መሻሻል የታየበት እንደነበር የውኃ እና ኢነርጅ ሚኒስቴር ዴኤታ አብርሀ አዱኛ (ዶ.ር ) ገልጸዋል።

የመጠጥ ውኃ ሽፋኑ ባለፈው ዓመት ከነበረው 67 ነጥብ 1 በመቶ ወደ 69 ነጥብ 5 በመቶ ከፍ ማለቱ በሪፖርቱ ቀርቧል።

እንደ ሀገር ከጠቅላላው ሕዝብ 74 ነጥብ 6 ሚሊዮኑ የመጠጥ ውኃ እያገኘ መኾኑንም ሚኒስቴር ዴኤታው ተናግረዋል።

በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የስትራቴጅክ ጉዳዮች ሥራ አሥፈጻሚ ዓለሙ መንገሻ በውኃ ሃብት አሥተዳደር፣ በመጠጥ ውኃ እና ሳኒቴሽን እንዲሁም በኢነርጅ ልማት ዘርፍ ላይ በበጀት ዓመቱ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን ገልጸዋል።

ከኢነርጅ ልማት ዘርፍ አንዱ በኾነው በኤሌክትሪክ ተደራሽነት 52 በመቶ መድረስ መቻሉም በሪፖርቱ ቀርቧል።

የድንበር እና ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ በተመለከተ 43 የሚደርሱ ሰነዶች እና ጥናቶች መሠራታቸው በሪፖርቱ ተገልጿል።

የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልል ውኃ እና ኢነርጂ ቢሮዎች እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸሙን እየገመገመ ይገኛል።

ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ኃይለኢየሱስ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በሕዝብ የተነሱ ቅሬታዎችን መፍታት በመጀመራችን በዞኑ አንጻራዊ ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ ችለናል” የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ኑርልኝ ብርሃኑ
Next articleየደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በልዩ ልዩ የትምህርት አይነቶች ያሰለጠናቸውን 885 ተማሪዎች አስመረቀ።