“በሕዝብ የተነሱ ቅሬታዎችን መፍታት በመጀመራችን በዞኑ አንጻራዊ ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ ችለናል” የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ኑርልኝ ብርሃኑ

22

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በምሥራቅ ጎጃም ዞን አሥተዳደር የዞን እና የወረዳ መሪዎች በ2016 ዓ.ም አፈጻጸም እና በክረምት ሥራዎች ዙሪያ ውይይት እያካሄዱ ነዉ።

በመድረኩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ኑርልኝ ብርሃኑ እንደገለጹት በዞኑ በተፈጠረው ቀውስ በርካታ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት መድረሱን አስታውሰዋል።

ይህንን ችግር ለመፍታት በተደረገ ርብርብ ዉጤታማ ሥራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።

“በሕዝብ የተነሱ ቅሬታዎችን መፍታት በመጀመራችን በዞኑ አንጻራዊ ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ ችለናል” ብለዋል። በሕዝብ እና በመንግሥት መካከል መቀራረብ መፍጠር እንደተቻለም ተነግረዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም ወደ ዘላቂ ሰላም ለማሸጋገር ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል” በምዕራብ ጎጃም ዞን የሽንዲ ከተማ ነዋሪዎች
Next articleሀገራዊ የመጠጥ ውኃ ሽፋን 69 ነጥብ 5 በመቶ መድረሱን የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ።