
ባሕር ዳር: ሐምሌ 6/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ከሐምሌ 4 እስከ 5/2016 ዓ.ም በተካሄደው የብሪስክስ አባል ሀገራት ፓርላሜንታዊ ፎረም ላይ ተሳትፏል፡፡
አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በፎረሙ ላይ ባደረጉት ንግግር “ኢትዮጵያ በብሪክስ አባል ሀገራት መካከል ምጣኔ ሃብታዊ፣ ፖለቲካዊ እና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እንዲጠናከር ትሠራለች” ብለዋል፡፡
አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ከፎረሙ ጎን ለጎን ከሩሲያ፣ አዘርባጃን እና ኢራን የልዑካን ቡድን መሪዎች ጋር ውይይቶችን አካሂደዋል፡፡
በውይይታቸውም በሀገራቱ መካከል የፓርላሜንታዊ ትብብርን ማጠናከር፣ ምጣኔ ሃብታዊ ግንኙነትን ማሳደግ እና ፖለቲካዊ አጋርነትን ማጎልበት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማኅበራዊ የትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!