
የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር “ሰላም ለሁሉም፣ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ ከመንግሥት ሠራተኞች ጋር የሰላም ኮንፍረንስ አካሂዷል።
የመንግሥት ሠራተኞች በሰጡት አስተያየት ስለ ሰላም መምከር ካልተቻለ ሰላም ሊመጣ እንደማይችል ገልጸዋል። ሰላምን ለማምጣት እንደ መንግሥት ሠራተኛ የሚጠበቅብን ምንድን ነው? ብሎ መጠየቅ ይገባልም ብለዋል። ችግሮችን በውይይት ባለመፍታታችን ክልሉ ለረጅም ጊዜ ሰላም አጥቶ መቆየቱን እና በኢኮኖሚ መጎዳቱን ጠቅሰዋል።
ሀሉም አካል በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ በመወያየት ክልላችን የሰላም አየር እንዲተነፍስ ማድረግ ይገባዋል ሲሉም ተናግረዋል። ሀገርን የማጽናት ኅላፊነት የሁሉም ስለኾነ የመንግሥት ሠራተኛውም ባገኘው አጋጣሚ ስለሰላም መምከር እና መስበክ እንደሚኖርበት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ።
ዘጋቢ: መስዑድ ጀማል
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!