
ባሕር ዳር: ሐምሌ 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) አገልግሎቱ ፍትሐዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን እውን ለማድረግ በሀገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት በኩል በርካታ ሥራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡
በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት 100 አዳዲስ የገጠር ከተሞች እና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ 116 የገጠር ከተሞች እና መንደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ተብሏል። በተጨማሪም በኦፍ ግሪድ ቴክኖሎጂ የኀይል አማራጭ ከዋናው ግሪድ ርቀው የሚገኙ ሁለት የገጠር ከተሞች እና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ መኾናቸው ነው የተገለጸው።
ለዚህም 1 ሺህ 160 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር፣ 1 ሺህ 588 ኪሎ ሜትር የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ እና 382 የዲስትሪቢዩሽን ትራንስፎርመሮች ተከላ ሥራ መከናወኑን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!