
ባሕር ዳር: ሐምሌ 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምዕራብ ደምቢያ ወረዳ “ሰላም ለሁሉም፣ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ ከመንግሥት ሠራተኞች፣ ከወጣቶች እና ከንግዱ ማኀበረሰብ ጋር የሰላም ኮንፈረንስ ተካሂዷል ፡፡
የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡት የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኅላፊ መሃሪዉ ርስቱ እንደገለጹት ከዚህ በፊት በተፈጠረው ችግር ምክንያት የወረዳው ሕዝብ ለዘርፈ ብዙ ችግሮች ተጋላጭ ኾኖል፡፡
በግጭቱ ምክንያት ማኀበረሰቡ ለሥነ ልቦናዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኀበራዊ ጫናዎች ተዳርጓል ያሉት ኅላፊው ካጋጠመው ችግር ለመውጣት ደግሞ በሰላም ኮንፈረንሱ የተቀመጠው የውይይት ሀሳብ እንዲሳካ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል ።
የውይይቱ ተሳታፊዎችም የሰላም ካውንስሉ የሰላም የመፍትሔ ሀሳብ የዘገየ ቢኾንም ተገቢ እና አስፈላጊ ነው ማለታቸውን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!