የቀረበው የሰላም አማራጭ ተግባራዊ እንዲኾን የበኩላቸውን እንደሚወጡ የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

12

ባሕር ዳር: ሐምሌ 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “ሰላም ለሁሉም፣ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ በደብረማርቆስ ከተማ የሰላም ኮንፈረንስ ተካሂዷል።

በሰላም እጦት ያገኘነው ጥቅም የለም፣ ልማታችን ወደ ኋላ ቀርቷል፣ ውድ የኾነው የሰው ሕይወት ጠፍቷል ያሉት የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች ይኽ እንዲቆም የተጀመረው የሰላም አማራጭ ተግባራዊ ሊኾን ይገባል ብለዋል። ለዚኽም የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል። የጸጥታ ችግሩ ሰው በሰላም ወጥቶ እንዳይገባ ስጋት ፈጥሯል ያሉት አስተያየት ሰጭዎች ሕግ እንዲከበር መንግሥት የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ መቀጠል አለበት ማለታቸውን ከከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በግጭቱ ምክንያት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ኪሳራ ደርሷል ያሉት በደብረማርቆስ ከተማ የተድላ ጓሉ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ መኮንን ደባሱ የቆሙ ፕሮጀክቶች እንዲጀመሩ፣ የክልሉ ኢኮኖሚ እንዲነቃቃ፣ መገዳደል እንዲቆም፣ የክልሉ ሕዝብ ጥያቄዎች በሰላማዊ ትግል እንዲፈቱ ጫካ የገቡ ወንድሞቻችን ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲመጡ ማኀበረሰቡ የሚጠበቅበትን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleግጭት ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍል የሚጎዳ በመኾኑ ሁሉም ለሰላም መሥራት እንዳለበት የሰሜን ጎንደር ዞን የመንግሥት ሠራተኞች አሳሰቡ።
Next articleየሰላም ካውንስሉ ያቀረበው የሰላም ጥሪ ውጤታማ እንዲኾን የበኩላቸውን እንደሚወጡ የጎንደር ከተማ የመንግሥት ሠራተኞች ተናገሩ።