በመጭው አምስት ዓመታት ኢትዮጵያን ወደ ዲጂታል ትግበራ የሚያሻግር ንድፈ ሃሳብ ይፋ ኾነ።

45

አዲስ አበባ: ሐምሌ 4/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚስቴር፣ በአውሮፓ ኅብረት የገንዘብ ትብብር የሚካሄደው የዲጂታል ትግበራ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2024 እስከ 2029 ወደ ተግባር እንደሚገባ ነው የተገለጸው።

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው የማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ.ር) ንድፈ ሃሳቡ በተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተመክሮበት ተግባራዊ ሲኾን የኢትዮጵያን መጻዒ ዕድል ወደ ብሩህ ተስፋ የሚያስገባ እንደሚኾን ነው የተናገሩት፡፡

ማኅበረሰቡም በተለያዩ ሕዝባዊ አገልግሎቶች ላይ ይደርስበት የነበረውን እንግልት የሚቀርፍ ስለመኾኑም ነው ያብራሩት። በመርሐ ግብሩ የአውሮፓ ኅብረት የዘርፉ የበላይ ጠባቂን ጨምሮ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው። የንድፈ ሃሳቡ የቀጣይ አምስት ዓመት አተገባበርን የተመለከተ ዝርዝር አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት እየተደረገበትም ይገኛል።

ዘጋቢ፡- ደረጀ አምባው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጸጥታ ችግሩ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ የበኩላቸውን እንደሚወጡ የሰሜን ጎጃም ዞን መምህራን ተናገሩ።
Next articleበሰሜን ወሎ ዞን “ሰላም ለሁሉም፣ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት የሰላም ኮንፈረንስ ተካሂዷል።