
ባሕር ዳር: ሐምሌ 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ)
በሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ወረዳ የመምህራን ኮንፈረንስ ተካሂዷል።
“ሰላም ለሁሉም፣ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልእክት ከ18 ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች በኮንፈረንሱ ተሳትፈዋል። የተከሰተው የጸጥታ ችግር ሰላማዊ በኾነ መንገድ እንዲፈታ የድርሻቸውን እንደሚያበረክቱ የኮንፈረንሱ ተሳታፊ መምህራን አረጋግጠዋል ፡፡
ተሳታፊዎች ትምህርት ለአንድ ሀገር መሰረት በመኾኑ የተከሰተውን የጸጥታ ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና የተቋረጠውን የትምህርት ሥራ ለመጀመር የድርሻቸውን እንደሚወጡ መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!