ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶች እና የምግብ ዓይነቶች መወገዳቸውን ጤና ቢሮ አስታወቀ።

16

ባሕር ዳር: ሐምሌ 4/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ከ100 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶች እና የምግብ ዓይነቶች መወገዳቸውን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል።

የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ጤና እና ጤና ነክ ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክተር ጌትነት ስንታየሁ እንዳሉት ቢሮው ለማኅበረሰቡ ከሚሰጠው አገልግሎት ባለፈ በክልሉ የሚገኙ የመንግሥት እና የግል የጤና ተቋማትን የቁጥጥር ሥራ ይሠራል። በዚህም በበጀት ዓመቱ ጊዜያቸው ያለፈባቸው እና ግምታቸው ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ የኾኑ መድኃኒታችን እና የምግብ ዓይነቶችን የማስወገድ ሥራ ተሠርቷል ብለዋል። በቁጥጥር ሂደቱ የተዘጉ ተቋማት መኖራቸውንም ገልጸዋል።

በተለይ በደሴ ከተማ አሥተዳደር ከ10 ዓመት በላይ በማስወገጃ እጥረት ምክንያት ተከማችተው የቆዩ የግብዓት ዓይነቶችን የማስወገድ ሥራ መሠራቱን ገልጸዋል። ማኅበረሰቡ የመድኃኒቶችን የመጠቀሚያ ጊዜ አይቶ እና መጠኑን ተረድቶ እንዲጠቀም አሳስበዋል። ማኅበረሰቡ የቁጥጥር ሥራውን እንዲያግዝም ጥሪ አቅርበዋል።

በአማራ ክልል የመድኃኒት ችርቻሮዎችን ጨምሮ 8 ሺህ 593 ተቋማት ይገኛሉ። ከዚህ ውስጥ 4 ሺህ 410 የግል ተቋማት መኾናቸውም ተገልጿል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ከ1 ሺህ 300 በላይ ጫካ የገቡ ኀይሎች ወደ ሰላማዊ ሕይዎት ተመልሰዋል” የደቡብ ጎንደር ዞን አሥተዳደር
Next articleለሕዝብ ሰላም እና ደኅንነት ሲባል ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ የመንግሥት ሠራተኛው የድርሻውን እንዲወጣ የምዕራብ ጎንደር ዞን አሥተዳደር አሳሰበ፡፡