የሰላም ካውንስሉ ጥረት እውን እንዲኾን መንግሥት በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ የራያ ቆቦ ወረዳ ነዎሪዎች ተናገሩ።

16

ባሕር ዳር: ሐምሌ 4/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ “ሰላም ለሁሉም፣ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልእክት የሰላም ኮንፍረንስ ተካሄዷል።

የመድረኩ ተሳፊዎችም መንግሥት ያቀረበው የሰላም አማራጭ ስንጠይቀው የነበረ ጉዳይ በመኾኑ በእኛ በኩል ደስተኞች ነን ብለዋል። ነገር ግን የሰላም ካውንስሉ ጥረት እውን እንዲኾን መንግሥት በትኩረት መሥራት አለበት ብለዋል። በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖች መንግሥት ያቀረበውን የሰላም አማራጭ በመቀበል ወደ ሰላም ምክክሩ እና ንግግሩ እንዲመለሱ ሊሠራ እንደሚገባም ተናግረዋል።

እንደ ዞኑ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን መረጃ ውይይቱን የመሩት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ መኮነን አጥናፋ የሰላም ካውንስሉ ጥረት ተግባራዊ እንዲኾን ሁሉም በጋራ ሊሠራ ይገባል ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleክላውድ ኮምፒውቲንግ ምንድን ነው?
Next article“ከ1 ሺህ 300 በላይ ጫካ የገቡ ኀይሎች ወደ ሰላማዊ ሕይዎት ተመልሰዋል” የደቡብ ጎንደር ዞን አሥተዳደር