
“ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት በጎንደር ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት ሠራተኞች የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ የሕዝብ ግንኙነት እና አደረጃጀት ዋና አማካሪ ቻላቸው ዳኘው “ለሰላም ሁላችንም ባለቤት መኾን ይገባናል” ብለዋል።
“የአማራ መጎሳቆል እና እርስ በእርስ መጠፋፋት ሊበቃ ይገባል” ያሉት አቶ ቻላቸው አሁን ላይ ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዞ ሰላምን ለማምጣት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባውም አስረድተዋል። የመንግሥት ሠራተኛው ለሰላም የበኩሉን አስተዋጽኦ ሊያበረክት እንደሚገባም አሳስበዋል። በሰላም ኮንፈረንሱ የከተማ አሥተዳሩ የመንግሥት ሠራተኞች እየተሳተፉ እንደኾ ከጎንደር ከተማ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!