“ሀገርን መስሪያ፣ ትውልድን መቅረጫ፣ ባሕል እና ወግን ማስተዋወቂያ ቀመሩ ሚዲያ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

60

ባሕር ዳር: ሐምሌ 4/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልእክት “ሚዲያ ለሀገር” በሚል መሪ ሃሳብ በተዘጋጀው መርሐ ግብር ላይ ዕውቅና የተቸራችሁ መገናኛ ብዙሃን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ ብለዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው በሀገር ግንባታ፣ በትውልድ ቅብብሎሽ፣ ታሪክን በመሰነድ እና መረጃን በማቀበሉ ረገድ የሚዲያ ድርሻ ትልቅ ነው፡፡

በመኾኑም ሚዲያዎች ለብሔራዊ ጥቅም፣ ለሀገር አንድነት እንዲሁም ማኅበረሰባዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ሥራዎች ላይ የበለጠ ትኩረት እንድትሰጡ አደራ እላለሁ ብለዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ሀገራዊ የገጠር መንገድ ትስስር ፕሮጀክት ተግባራዊ ሊደረግ መኾኑ ተገለጸ።
Next article“የአማራ መጎሳቆል እና እርስ በእርስ መጠፋፋት ሊበቃ ይገባል” የጎንደር ከተማ አሥተዳደር