በስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ሐምሌ 15 /2016 እንደሚጀምር ተገለጸ።

18

ባሕር ዳር: ሐምሌ 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ጽሕፈት ቤት ኅላፊ ኤፍሬም ወንዴ በፓርኩ በ4 ነጥብ 7 ሔክታር መሬት ላይ 21ሺህ ችግኞችን ለመትከል እቅድ እንደተያዘ ተናግረዋል።

ለዚህም የችግኝ ማፍላት ሥራ፣ የቦታ መረጣ፣ ጉድጓድ ቁፋሮ እና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እንደተከናወኑ ገልጸዋል። ችግኝ ተከላው ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም እንደሚጀምርም አሳውቀዋል፡፡ ኅላፊው ጨምረውም ችግኝ ተከላዉ በአካባቢው ማኀበረሰብ፣ በባለሙያዎች፣ በሥራ ኀላፊዎች እና በበጎ አድራጎት ድረጅቶች እንደሚከወን ተናግረዋል፡፡

ባለፈዉ ዓመት 25 ሺህ ችግኞች እንደተተከሉ የገለጹት አቶ ኤፍሬም ወንዴ የተተከሉ ችግኞች በአግባቡ እንዲጸድቁ እና ነባር ደኖችም ከእሳት አደጋ እንዲጠበቁ በየቀበሌዉ ለተመረጡ አባወራዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና እንደተሠጣቸዉ አቶ ኤፍሬም ተናግረዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ወቅት ሥራችን ያስቀመጥነውን ግብ በሚያሳካ መልካም አጀማመር ላይ ይገኛል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next article“እንደ ዲፕሎማት በሕዝብ መታመን እና የብሔራዊ ኩራት ምንጭ መኾን ተገቢ ነው” አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ