
ባሕር ዳር: ሐምሌ 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኅብረተሰቡ የችግኝ ተከላ ተነሳሽነት ከፍተኛ መኾኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ተናግረዋል። በዛሬው ዕለትም በጫካ ፕሮጀክት ስፍራ የአፕል ችግኞችን መትከላቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። በአካባቢው የተደረገውን የዘንድሮውን ችግኝ ተከላ ለየት የሚያደርገው ቀድሞ የነበረው የባህርዛፍ ሽፋን ተወግዶ በሀገር በቀል የእርከን ሥራ እና ተክል የተተካ መሆኑን ገልጸዋል።
ከሀረር አካባቢ እና ከኮንሶ የመጡ ሕዝቦች አፈር እንዳይሸረሸር የሚያደርገውን ጊዜ የማይሽረው ክህሎታቸውን አካፍለውናል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ። በከተሞች የምንሠራውን የአረንጓዴ አሻራ ጥረቶቻችንን በጋራ በማስፋፋት የአዲስ አበባን አረንጓዴ ሽፋን መጨመር እንችላለን ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!