
ባሕር ዳር: ሐምሌ 3/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር በሁሉም ክፍለ ከተሞች ከነጋዴው ማኅበረሰብ ጋር የሚመክር የሰላም ኮንፈረስ ተካሂዷል።
“ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት በደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር በየደረጃው ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የሚመክር የሰላም ኮንፈረንስ ተካሂዷል።
የኮንፈረሱ ተሳታፊዎች ችግሮችን በውይይት እና በንግግር መፍታት እንደሚገባ በማንሳት ሰላም የሁሉንም ወገኖች ርብርብ ስለሚጠይቅ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እና ክልሉን ወደ ተሟላ ሰላም መመለስ ያስፈልጋል ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!