
ደብረ ብርሃን: ሐምሌ 3/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በደብረ ብርሀን ከተማ “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ቃል ከመንግሥት ሠራተኞች ጋር የሰላም ኮንፈረንስ ተካሂዷል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት ያጋጠመን የሰላም እጦት ማኅበረሰቡን ለበርካታ ውስብስብ ችግሮች ዳርጎት ቆይቷል ብለዋል። የተገኘው አንጻራዊ ሰላም ቀጣይነት እንዲኖረው ለማስቻል ከመንግሥት ሠራተኛው ጋር ውይይት ማድረግ ማስፈለጉንም ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፓለቲካ ዘርፍ ምክትል ኀላፊ አቶ ተክለዩሃንስ ኃብረጊዮርጊስ በበኩላቸው ያጋጠመው የሰላም ችግር በኅብረተሰቡ ላይ ያሳደረው የሥነ ልቦና ቀውስ ከፍተኛ ነው ብለዋል። “ችግሮች በውይይት እና በንግግር እንዲፈቱ የመንግሥት ሠራተኛው ሀገራዊ ኀላፊነት አለበት” ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ለዚህም ሁለቱን ወገኖች ወደ ጠረጴዛ ለማምጣት ከፊት መሰለፍ ይኖርባቸዋል ብለዋል።
ዘጋቢ፡- ፋንታነሽ መሐመድ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!