4 ሺህ 200 የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ እየወሰዱ ነው።

13

እንጅባራ: ሐምሌ 03/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ.ር) ዩኒቨርሲቲው ከአዊ ብሔረሰብ አስተዳደርና መተከል ዞን የተመደቡ 9 ሺህ 921 ተፈታኝ ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል።

በዩኒቨርሲቲው ለመጀመሪያው ዙር የ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና የተመደቡ 4 ሺህ 200 የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናቸውን በሰላም እየወሰዱ መኾናቸውንም ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።

ተማሪዎችን በሥነ ልቦና ማዘጋጀት እና ለተማሪዎች አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎችን በትምህርት ሚኒስቴር መስፈርት መሠረት ቅድመ ሁኔታዎችን የማሟላት ሥራ በቅድመ ዝግጅት ወቅት ተከናውነዋልም ነው ያሉት።

ዩኒቨርሲቲው በሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የተመደቡ ከ5 ሺህ 700 በላይ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ለመቀበል ከወዲሁ መዘጋጀቱንም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።

ዘጋቢ:- ሳሙኤል አማረ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኮምቦልቻ ከተማ ተለዋጭ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው።
Next articleበግብርናው ዘርፍ ውስጥ የሚገኙ ፕሮጀክቶች ያላቸውን ሃብት ያለምንም ብክነት መጠቀም አለባቸው።