
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር በባቲ ወረዳ ሰላጤ ቀበሌ ‘ሚአ’ ወንዝ ላይ በ5 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በጀት ተገንብቶ የተጠናቀቀ 95 ሜትር ተንጠልጣይ ድልድይ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
የብሔረሰብ አሥተዳደሩ መንገድ መምሪያ መረጃ እንደሚያሳየው የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ ከሄልቪታስ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የተሠራ ፕሮጀክት ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!