
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሀራ ከተማ አሥተዳደር “ሰላም ለሁሉም፣ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ ከመንግሥት ሠራተኞች ጋር ኮንፈረንስ ተካሄዷል።
የሀራ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሙሐመድ ስዒድ ሰላም ለሁሉም መሰረት በመኾኑ ሁላችንም ለሰላም በትኩረት ልንሠራ ይገባል ብለዋል። ከንቲባው አያይዘውም ማንኛውም ጥያቄ የሚመለሰው በሰላማዊ መንግድ በመኾኑ ሁሉም አካል ለሰላም ካውንስሉ ጥሪ መልካም ምላሽ ሊኖረው እንደሚገባ አመላክተዋል።
የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የሰላም ካውንስሉ መቋቋሙ በጣም አስፈላጊ እና ጠቃሚ መኾኑን ገልጸዋል። በመኾኑም አስፈላጊውን ሁሉ እገዛ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!