በአሁኑ ጊዜ ዘጠኝ ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤታቸውን በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

265

የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ ከጤና ሚኒስቴር የተሰጠ መግለጫ::

• በአሁኑ ጊዜ ዘጠኝ ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤታቸውን በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
• ከቀን 13/2012 ዓ.ም ሌሊት 6፡00 ጀምሮ ማንኛውም ከውጭ ሀገር የሚመጣ መንገደኛ በሆቴል ውስጥ ለ14 ቀናት ተለይቶ እንዲቆይ በተወሰነው መሠረት ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ወደ ሀገራችን የገቡ ከ519 መንገደኞች በተመረጡ ሆቴሎች ማቆያ ውስጥ ይገኛሉ፡፡
• በኢትዮጵያ 12 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው መሆኑ መገለጹ ይታወሳል፡፡ ከ12 ታማሚዎች ውስጥ ሁለቱ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡ ሌሎች ታማሚዎች በለይቶ የሕክምና መስጫ ማዕከል የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛሉ፤ ሁሉም ታማሚዎች በመልካም ጤንነት ላይ ናቸው፡፡
• ወደ ሀገር ውስጥ መግቢያ ጣቢያዎች እየተደረገ የሚገኘው ምርመራ ተጠናክሯል፤ 668 ሺህ 476 ሰዎች በሙቀት መለያ አልፈዋል፡፡
• በሙቀት መለያ ካለፉት ውስጥ 12 ሺህ 245 ያህሉ በሽታውን ሪፖርት ካደረጉ ሀገራት የመጡ ናቸው፡፡
• በአሁኑ ጊዜ 1 ሺህ 923 የሚሆኑት ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ሰዎች ለ14 ቀን የጤና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛሉ፡፡ 1ሺህ 772 የሚሆኑት ለ14 ቀናት ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተው የኮሮና በሽታ ምልክት ያልታየባቸው በመሆኑ ክትትላቸው ተቋርጧል፡፡
• እስካሁኑ ሰዓት 576 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸዋል፤ 555 ሰዎች ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡
• ከዚህ በፊት ከተሠራጩት የሕክምና መስጫ ግብዓቶች በተጨማሪ ከ2 ሚሊዮን በላይ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ለሁሉም ክልሎች ተሠራጭቷል፡፡
• ኅብረተሰቡ የኮሮና ቫይስን (ኮቪድ-19) ለመከላከል የወጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ እንዲያደረግ ጤና ሚኒስቴርና የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጥብቅ አሳስበዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም 952 ፤ በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ማግኘት ይቻላል፡፡

Previous articleከ873 ሺህ በላይ ሐሰተኛ የአሜሪካን ዶላር በቁጥጥር ስር ዋለ።
Next articleታራሚዎች ራሳቸውን ከኮረና ቫይረስ ስርጭት እንዲከላከሉ የቅድመ ጥንቃቄ ሥራ እያከናወነ መሆኑን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ማረሚያ ቤቶች መምሪያ አስታወቀ፡፡