
ባሕር ዳር: ሐምሌ 2/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን አላማጣ ከተማ የተደረገው ውይይት በአካባቢው ስላለው ወቅታዊ የሰላም ሁኔታ እና ተፈናቅለው የነበሩ ነዋሪዎችን ወደ ቀያቸው በሚመለሱበት ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው።
የሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ብርጋዲየር ጄኔራል በላይ አየለ ተፈናቅለው የነበሩ የአላማጣ ወረዳ ነዋሪዎች ወደ ቤት ንብረታቸው በመመለስ ሰላማዊ ሕይዎታቸውን ማስቀጠል እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎች እና የሃይማኖት አባቶች በበኩላቸው የሪፐብሊካን ጥበቃ ኃይል እና ሌሎችም የጸጥታ አካላት ወደ ስፍራው ከተሠማሩ በኋላ አካባቢው ፍጹም ሰላም መኾኑን ገልጸዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!