የመጀመሪያው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው፡፡

60

አዲስ አበባ: ሐምሌ 2/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአፍሪካ ከተሞች ፎረምን በተመለከተ የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቷል።

ከነሐሴ 29/2016 ዓ.ም አስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም የሚቆይ በአፍሪካ የመጀመሪያው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ገልጸዋል፡፡ ፎረሙ በከተሞች መካከል ዘላቂ ልማት እንዲረጋገጥ እና በትብብር ሠርቶ ማደግ የሚያስችል እንደኾነም ነው የገለጹት።

የበለጸገች እና እርስ በእርስ የተሳሰረች አፍሪካን እውን ለማድረግ አጀንዳ 2063 ቀርፃ እየሠራች ስለመኾኑ ገልጸዋል፡፡ የፎረሙ መዘጋጀት ዋና ዓላማውም አጀንዳው እንዲሳካ መኾኑን ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ ተናግረዋል። የመጀመሪያውን የአፍሪካ ከተሞች ፎረም የአፍሪካ ኅብረት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በመቀናጀት ያዘጋጁት መኾኑንም ጠቁመዋል።

በመግለጫው ላይ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እና የአፍሪካ ኅብረት መሪዎች እንዲሁም የከተሞች ከንቲባዎች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፡- ቤተልሄም ሰለሞን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
Next articleየክልሉ የሰላም ካውንስል ባቀረበው የሰላም ጥሪ መሰረት 20 ታጣቂ ኃይሎች ማኅበረሰቡን ተቀላቀሉ።