
ባሕር ዳር: ሐምሌ 2/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የዓለም ከተማ አሥተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኅላፊ ታጠረወርቅ ገለታ “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልእክት ለከተማ እና የቀበሌ መሪዎች ሰነድ ቀርቦ ውይይት እንደተደረገ ገልጸዋል።
ተመሳሳይ ውይይት ከሕብረተሰቡ ጋር እንደሚካሄድም ጠቁመዋል። የዓለም ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አበበ ተሰማ ኮንፈረንሱ ለሰላም መስፈን ያለውን ፋይዳ ተናግረው ሁሉም አካል ለሰላም መረጋገጥ የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል።
አቶ አበበ ተሰማ ከሕብረተሰቡ ጋር የሚካሄደው ኮንፍረንስ በቅርብ እንደሚካሄድ ተናግረዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!