
ባሕር ዳር: ሐምሌ 2/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሰላም አማራጩን የሚቀበሉ ታጣቂዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።
በዞኑ ላይ አርማጭሆ ወረዳ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 10 ታጣቂዎች የሰላም አማራጩን ተቀብለው ማኅበረሰቡን ተቀላቅለዋል። መንግሥት ላደረገላቸው ይቅርታ ያመሰገኑት ታጣቂዎቹ በቀጣይ ወደ መደበኛ ሕይዎታቸው ተመልሰው የአካባቢያቸውን ሰላም እና ልማት ለማረጋገጥ እንደሚሠሩም ተናግረዋል።
እንደ ማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሐንግሥት ኮምዩኒኬሽን መምሪያ መረጃ ወደ ሰላማዊ ሕይዎት የተመለሱት ታጣቂዎች የሚፈጠሩ ችግሮችን በውይይት መፍታት የስልጣኔ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!