ወጣቶች በሀገራዊ ምክክሩ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ።

15

ባሕር ዳር: ሐምሌ 2/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያዘጋጀው የወጣቶች የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ ባስተላለፉት መልዕክት ወጣቶች የመነጋገር እና የመደማመጥ ባሕልን በማጎልበት በሀገራዊ ምክክሩ ሚናቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ ለሰላም እና ለተረጋጋ የሀገረ መንግሥት ግንባታ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ መኾኑንም አክለዋል፡፡

በመድረኩ በትውልድ መካከል መኖር ስለሚገባው ምክክር እንዲሁም በሀገራዊ ምክክሩ የወጣቶችን ሚና ማሳደግ ስለሚቻልባቸው መንገዶች በኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች የውይይት መነሻ ሃሳብ ቀርቧል። የመድረኩ ተሳታፊ ወጣቶችም በቀረቡላቸው የመነሻ ሃሳቦች ላይ ውይይት የሚያደርጉ ይኾናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በምክክር መድረኩ ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ ከ200 በላይ ወጣቶች እየተሳተፉ መኾኑን ከሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የሰላም አማራጭን መከተል እንደሚገባ የእንጅባራ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ።
Next articleበአለፋ ወረዳ የመንግሥት ሰራተኞች የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።