
ባሕር ዳር: ሐምሌ 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የተለያዩ ከተማ ከንቲባዎች በአዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር የልማት ሥራዎችን ነው እየጎበኙ የሚገኙት።
የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤም በአዲስ አበባ እየተሠሩ ባሉ እና በተጠናቀቁት የልማት ሥራዎች ዙሪያ ከንቲባዎች ገለጻ አድርገዋል። ጉብኝቱን ያዘጋጁትም የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በጋራ በመኾን ነው።
በጉብኝቱ ላይ የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ከከንቲባዎች ጋር በኮሪደር ልማቱ ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉም ተብሏል። የጉብኝቱ ዓላማም ከአዲስ አበባ ተሞክሮ በመውሰድ የልማት ሥራዎችን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማስፋት እንደኾነም ተገልጿል።
ዘጋቢ፡- ራሄል ደምሰው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!