
ባሕር ዳር: ሐምሌ 1/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኩታ ገጠም እርሻ ሥራ እየተስፋፋ የመጣ ተግባር መኾኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሉት የዚህ ክረምት የእርሻ ዕቅድን ሊያሳካ የሚችል ሰፊ እንቅስቃሴ ስለመጀመሩ ነው ያብራሩት። ሥራውም መጠናከር እንደሚገባው ነው ያስገነዘቡት። በዚህ ዓመት ከ24 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በኩታ ገጠም ለማረስ ዕቅድ እንዳለም ተናግረዋል።
ይህን ዕቅድ ለማሳካት ከዝናቡ ጋር መሽቀዳደም እንደሚገባም አሳስበዋል። የኩታ ገጠም ሥራ መሥራት እና ዘመናዊ መንገድን መከተል እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት። ይህ ተግባር በምግብ ራስን ለመቻል የሚደረገውን ጥረት የሚያሳካ እንደኾነም ገልጸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!