
ባሕር ዳር: ሐምሌ 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ)
በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ እና ለአብሮነት በሚል መሪ ቃል የክረምት በጎ አድራጎት ተግባር የማስጀመሪያ መርሐ ግብር በጎንደር ከተማ ተካሂዷል።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሃይ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎች በከተማው እየተከናወኑ መኾኑን ጠቅሰዋል። የክረምት በጎ አድራጎት ሥራ በመሰረተ ልማት ሥራዎች እና በትምህርት ሥራዎች እንዲሁም የአቅመ ደካሞችን ቤት እድሳት እንደሚያካትት አሳውቀዋል።
የጎንደር ከተማ ወጣቶች በተለያዩ አደረጃጀቶች በመሳተፍ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን እየሠሩ ነው ብለዋል። ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ወጣቶች እያከናወኑ ያሉት መልካም ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባ መኾኑን ጠቁመዋል።
እድሳት የተደረገላቸው ወገኖች በከባድ ችግር ውስጥ እንደነበሩ አስታውሰው የእድሉ ተጠቃሚ በመኾናቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል። ለበጎ አድራጊዎች ምስጋናም አቅርበዋል።
ዘጋቢ ፡-ምስጋናው ከፍያለው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!