ወሌ ሾይንካ መንግሥትና የሃይማኖት መሪዎችን ተችተዋል፡፡

153

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 16/2012 ዓ.ም (አብመድ) ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የናይጄሪያ መንግሥት እየሰጠ ያለውን ምላሽና የሃይማኖት መሪዎችን የኖቤል ሥነ-ጽሑፍ ሎሬቱ ወሌ ሾይንካ ተችተዋል፡፡ በሳምንቱ አንዳንድ ሰባኪዎች መንግሥት የሚያስተላልፋቸውን የአካላዊ መራራቅ መመሪያዎች ችላ በማለት ለእሑድ አገልግሎት በሺዎች የሚቆጠሩት ሰዎች ወደታደሙባቸው ጉባኤዎች ማቅናታቸው ተገቢ አለመሆኑን አመላክተዋል፡፡

የናይጄሪያ መንግሥት በቂ የለይቶ ማቆያ ማዕከላት፣ ጥሩ የመድኃኒት ክምችት ያላቸው መድኃኒት ቤቶችና የምርምር ማዕከላት ሊኖሯት ይገባ እንደነበር በማሳትም ሎሬቱ ተችተዋ፡፡

ፕሮፌሰር ሾይንካ ከአሜሪካ ከተመለሱ በኋላ ራሳቸውን ለዘጠኝ ቀናት በለይቶ ክትትል ማድረጊያ ውስጥ አቆይተዋል፡፡

በናይጄሪያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ይህ ዘገባ እስከተሰናዳበት ጊዜ ድረስ 46 ደርሷል፤ የአንድ ሰውም ሕይወትም ተመዝግቧል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ታዋቂ ሰዎችን በአፍሪካ ምድር መንጠቅ ጀምሯል፤ ካሜሮናዊው የሳክስፎን ተጨዋች ማኑ ዲባንጎ ትናንት አርፏል፡፡ በአፍሪካ 46 ሀገራት ላይ ቫይረሱ መግባቱ ተረጋግጧል፤ 2 ሺህ 475 ሰዎች ደግሞ በአህጉሩ ቫይረሱ እንዳለባቸው ታውቋል፤ 64 ሰዎችም ሕይወታቸው አልፏል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

በኪሩቤል ተሾመ

Previous article“ዋናው መፍትሄ መከላከልና መከላከል ብቻ ነው፡፡” የአማራ ሀኪሞች ማኅበር
Next articleስለ ኮሮና ቫይረስ ዕለታዊ መረጃዎች