የወንበረማ የመንግሥት ሰራተኞች የወረዳቸውን ሰላም ለመመለስ ድርሻችን ከፍተኛውን ነው አሉ።

17

ባሕር ዳር: ሐምሌ 1/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በምዕራብ ጎጃም ዞን የወንበርማ ወረዳ የመንግሥት ሰራተኞች “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልእክት የሰላም ኮንፍረንስ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ ወረዳውን ወደነበረበት ሰላም ለመመለስ የመንግሥት ሰራተኛው ከፍተኛውን ድርሻ መውሰድ እንደሚገባው መግባባት ላይ ተደርሷል።

ኅብረተሰቡ ጥያቄዎች እንዲፈቱ፣ ግጭት እንዲቆም፣ ሰላም እንዲመጣ፣ የኑሮ ውድነት እንዲስተካከል እንዲሁም ሌሎች የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ እየጠየቀ ቢኾንም መፍትሄ ግን አላገኘም ያሉት የመንግሥት ሰረተኞች መንግሥት ጥያቄዎችን እንዲፈታ ጠይቀዋል።

አሁን ባለው የኑሮ ውድነት የመንግሥት ሰራተኛው በከፍተኛ ሁኔታ እየተጎዳ በመኾኑ መንግሥት ይህን ችግር መሠረት ያደረገ መፍትሄ እንዲያመጣ መጠየቃቸውን ከዞኑ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበባሕር ዳር ከተማ ሁሉም ክፍለ ከተሞች “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ቃል የመምህራን የሰላም ኮንፈረንስ ተካሄደ።
Next article“ምክር ቤቶች የዜጎችን ሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበራቸውን የመቆጣጠር ሕገ መንግሥታዊ ግዴታ አለባቸው” አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ