“የአራት ኪሎ-ቀበና-ኬንያ ኤምባሲ ኮሪደር ሥራ ተጠናቅቋል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

26

ባሕር ዳር: ሐምሌ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዳሉት የአራት ኪሎ-ቀበና-ኬንያ ኤምባሲ ኮሪደር ሥራ ተጠናቅቋል፤ አካባቢውን አረንጓዴ የማድረግ ጥረቱ በጉልህ ይታያል ነው ያሉት። ባለፉት ሳምንታት የምሽቱን ውበት እንዳደነቅነው ዛሬ ደግሞ የማለዳን እይታ በኮሪደር ልማታችን ተመልክተናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ለስኬቱ በሥራው ለተሳተፉት የከተማው አሥተዳደር እና በሙሉ ፈቃድ ለተሳተፉ የግሉ ሴክተር ምሥጋና ይገባል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የከተማችንን የመኪና ማቆሚያ እጥረት የሚቀርፉ የፓርኪንግ ቦታዎች ተገንብተዋል ነው ያሉት። የእግር ጉዞን የሚያበረታቱ የእግረኛ መንገዶች ተስፋፍተው መሠራታቸውንም ገልጸዋል።

ይህን ባሕል መንከባከብ እና ማሳደግ ይገባል። ሁላችንም ህልው ለኾነው አዲስ መልክ ጠባቂዎች መኾን አለብን ብለዋል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልእክት።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“አሕመድ አሊ ፅንፈኝነትን በሀቅ እና እውነት ላይ ኾኖ የሞገተ ጀግና፤ ለሕዝብ አብሮነት ከልብ የሠራ እውነተኛ መሪ ነበር” ምክትል ርዕሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)
Next article“በክልሉ የሰላም ካውንስል የቀረበው የሰላም አማራጭ እና የድርድር ሀሳብ ሰላምን ለማረጋገጥ እድል የሚፈጥር ነው” የሰላም ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች