ባሕር ዳር: ሐምሌ 1/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ጎጃም ዞን ስር ባሉ የተለያዩ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደር ትናንት ሕዝባዊ የሰላም ኮንፈረስ ተካሂዷል።

26

በሰሜን ጎጃም ዞን ይልማ ዴንሳ፣ ጎንጅ ቆለላ፣ ሰሜን አቸፈር፣ ሰሜን ሜጫ፣ ደቡብ አቸፈረ ወረዳዎች እና ዱር ቤቴ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ቀበሌዎች “ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ የሰላም ኮንፈረንስ ተካሂዷል።

የሰላም ኮንፈረንሱ በዞኑ ሌሎች ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮችም መካሄዱን የጠቆመው የክልሉ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ የኮንፈረሱ ተሳታፊዎቹ “የተጀመረው ዘላቂ ሠላምን የማስፈን እንቅስቃሴ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት” ማለታቸውን አመላክቷል።

በኮንፈረንሱ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ምሁራን፣ አርሶ አደሮች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች እና አባላት ሌሎችም የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። በሰላም ኮንፈረንስ መድረኩ በየአካባቢው የሚታዩ ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ችግሮችን ለመፍታት የሰላም ኮንፈረንሱ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ታምኖበታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በውጤታማነት የመምራት ባሕል ተቋማዊ እንዲኾን የሕዝብ እንደራሴዎች ሚና ከፍተኛ ነው” ጋሻው አወቀ (ዶ.ር )
Next article“አሕመድ አሊ ፅንፈኝነትን በሀቅ እና እውነት ላይ ኾኖ የሞገተ ጀግና፤ ለሕዝብ አብሮነት ከልብ የሠራ እውነተኛ መሪ ነበር” ምክትል ርዕሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)