ባሕር ዳር: ሰኔ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬ አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች በተመረጡ 33 ከተሞች “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ ሀገር አቀፍ ሩጫ ተካሂዷል።
ስለሰላም የተካሄደውን እና በሰላም የተጠናቀቀውን ስኬታማ ሩጫ አስመልክቶ ለኢትዮጵያዊያን ምስጋና ያቀረቡት የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዷለም “ሰላም፣ ፍቅር እና አንድነት ኢትዮጵያን ያሻግራሉ” ብለዋል።
ኢትዮጵያዊያን ለሰላም ያለንን ቁርጠኝነት ለመላው ዓለም አሳይተናል ያሉት የሰላም ሚኒስትሩ ሰላም ለመኾን ብቸኛው እና አማራጭ የሌለው መንገዳችን ሰላም እራሱ ብቻ ነው ብለዋል።
በመኾኑም በዛሬው የሰላም እሩጫ ለሰላም የማንከፍለው መስዋዕትነት እንደሌለ በተግባር ላሳያችሁ ድንቅ ኢትዮጵያን በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ነው ያሉት።
ሁሉም የሀገራችን ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ለሀገራችን ሰላም ላሳያችሁት ተነሳሽነት እና ቁርጠኝነት እጅግ አደንቃለሁ ያሉት አቶ ብናልፍ ሰላሟ የበዛ እና የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለማስቀጠል ዛሬም ነገም በትጋት እና በጋራ እንሰራለን ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
“ሰላም፣ ፍቅር እና አንድነት ኢትዮጵያን ያሻግራሉ” አቶ ብናልፍ አንዷለም