
ባሕር ዳር: ሰኔ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን የሚወስዱ ተማሪዎች ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መግባት ጀምረዋል።
በዚህ ዓመት በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ 5 ሺህ 562 ተማሪዎች ተገኝተው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን እንደሚወስዱ ታውቋል።
ፈተናውን ከሚወስዱ ተማሪዎች መካከል 3 ሺህ 311 ሴቶች መኾናቸው ነው የተብራራው።
የሰሜን ሽዋ ዞን ትምህርት መምሪያ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ካምፖስ ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች እንዳሉም ገልጿል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
