“አሁናዊ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት መመካከር ወሳኝ ነው” የአለፋ ወረዳ የሰላም ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች

33

ባሕር ዳር: ሰኔ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በአለፋ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች “ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት የሰላም ኮንፈረንስ ተካሂዷል።

በሰላም ኮንፈረንሱ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና ሌሎችም የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊዎች ናቸው።

ተሳታፊዎቹ በዞኑ የሚታዩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ችግሮችን ለመፍታት የሰላም ኮንፈረንሱ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ነው ያሉት።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ እንዳለው የሰላም ኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች አሁናዊ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት መመካከር ወሳኝ ነው።

የዞኑ ሕዝብ በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው፣ በልማቱ እና በሰላሙ ተጠቃሚ የሚኾንበትን አቅጣጫ በማስቀመጥ ሊሠራ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሁሉም ጥያቄዎቻችን ሊመለሱ የሚችሉት ቀየው ሰላም ሲኾን ነው” የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች
Next article“ሰላም በመጥፋቱ ከማንም በላይ የተጎዳው የጎንደር ከተማ ሕዝብ ነው” የሰላም ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች