
ባሕር ዳር: ሰኔ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በደባርቅ ከተማ የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው። በዚህ ኮንፈረንስ ላይ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ የከተማዋ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ነው።
ነዋሪዎቹ እያካሄዱት ባለው ምክክር ላይ እንዳሉት አካባቢው ላይ ሰላም አለመኖሩ ዘርፈ ብዙ ጉዳቶችን እያስከተለ ነው።
በማኅበራዊም ኾነ በኢኮኖሚው ዘርፍ ግጭቱ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን አስታውሰዋል።
ይህን ችግር ለመቅረፍ ብቸኛው አማራጭ ውይይት ነው ያሉት ነዋሪዎቹ በውይይት እና በምክክር የማይፈታ ችግር እንደማይኖር ነው ያስረዱት።
“በክልሉም ኾነ በየአካባቢያችን ብዙ ሊመለሱ የሚገባቸው ጥያቄዎች አሉ፤ ሁሉም ጥያቄዎቻችን ሊመለሱ የሚችሉት ግን ቀየው ሰላም ሲኾን ነው” ብለዋል
የሰሜን ጎንደር ዞን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ እንዳለው ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት አሁን እየኾነ ያለው ሕዝብን ከመጉዳት የዘለለ መፍትሄ እንደማያመጣ ተገንዝበው ሰላምን እንዲመርጡ ጠይቀዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
