ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት ለሕዝባቸው ሰላም ሲሉ ለውይይት እንዲቀርቡ የደብረብርሃን ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ።

23

ባሕር ዳር: ሰኔ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረብርሃን ከተማ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ሰላም ላይ እየመከሩ ነው። ላለፉት ወራት በአካባቢው ያለውን የሰላም እጦት ወደ ነበረበት ለመመለስ ውይይት አስፈላጊ መኾኑን ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል። ግጭቱ የሕይዎት እና የንብረት ጥፋት ማስከተሉን የገለጹት ነዋሪዎቹ ግጭቱ ማብቃት እንዳለበት ነው ያሳሰቡት።

ሁሉም አትራፊ የሚኾነው ከሰላም በመኾኑ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት ለሕዝባቸው ሰላም ሲሉ ለውይይት እንዲቀርቡ ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል።
እየተካሄደ ያለው ግጭት የደብረ ብርሃን ከተማን ጎድቷታል ያሉት ነዋሪዎቹ ለከተማዋ ዕድገት ሁሉም ተቀራርቦ እንዲሠራ ነው ያስገነዘቡት።

የዞኑ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን እንዳለው በደብረብርሃን ከተማ በእምዬ ምኒልክ ክፍለ ከተማ በ6 ቀበሌዎች “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት ነው የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ የሚገኘው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።
Next article“ሁሉም ጥያቄዎቻችን ሊመለሱ የሚችሉት ቀየው ሰላም ሲኾን ነው” የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች