
ባሕር ዳር: ሰኔ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ በሚገኘው ኮንፈረንስ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና ሌሎችም የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊዎች ናቸው።
በከተማው የሚታዩ ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና የጸጥታ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሰላም ኮንፈረንሱ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረውም ተገልጿል። በክልል ደረጃም ኾነ በከተማው እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ወጥ የኾነ ለሕዝብ የሚጠቅም አመለካከት በመያዝ የከተማውን ብሎም የክልሉን ሕዝብ በሁለንተናዊ መንገድ ተጠቃሚ ለማድረግ ኮንፈረንሱ ጠቀሜታው የጎላ መኾኑም ተገልጿል።
ኮንፈረንሱ በቀጣይ በክፍለ ከተማ ደረጃ እንዲሁም በከተማ አስተዳደር ደረጃ በሁሉም ማኅበራዊ መሰረት እንደሚካሄድ ከከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
