
ባሕር ዳር: ሰኔ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ተጠሪ ጽሕፈት ቤት አዘጋጅነት”ከተረጅነት ወደ ምርታማነት፤ ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ነው።
በሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ልማት የንቅናቄ መድረኩ ተቀዳሚ ዋና አሥተዳደሪ ኃይሉ ግርማይን ጨምሮ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ፣ የየወረዳዎችና ከተማ አሥተዳደሮች ከፍተኛ መሪዎችና ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት እየተካሄደ ነው።
እንደ ብሔረሰብ አሥተዳደር የቀነሰውን ምርታማነት ለመጨመርና የተረጅነት መንፈስን ለመቀነስ አምራች መሬቶችን በዘላቂነት ማልማት እንደሚገባ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ተቀዳሚ ዋና አስተዳዳሪ ኃይሉ ግርማይ ተናግረዋል።
መንግሥትና ሕዝብ በመተባበር የወል መሬቶችን ምርት እንዲሠጡ በማድረግ ተረጅነትን መቅረፍ ይገባልም ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
