የሰላም ኮንፈረንስ በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ እየተካሄደ ነው።

47

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ፤ ወቀሎ አንጾኪያ ቀበሌ “ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

ባለፉት ወራት በክልሉ በተከሰተው የሰላም እና የፀጥታ ችግር በሕይወት እና ንብረት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሷል።ችግሩ ኢኮኖሚውንም በእጅጉ ጎድቶታል። ይህን ችግር ለማስወገድ ሰላምን ማጽናት አስፈላጊ ኾኖ በመገኘቱ የሰላም ኮንፈረንስ መዘጋጀቱ ነው የተገለጸው።

በኮንፈረንሱ መንግሥት ያመጣውን የሰላም አማራጭ በመጠቀም ሰላምን ወደነበረበት መመለስ እና ልማትን ማፋጠን እንደሚገባም ነው የተብራራው። ሰላምን ለማስፈን ሁሉም ኀላፊነት እንዳለበትም ተገልጿል።
የአካባቢው ማኅበረሰብም በኮንፈረንሱ በንቃት እየተሳተፈ ነው።

የሰሜን ሽዋ ዞን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ እንዳለው የሰላም ኮንፈረንሱ በለሚ 01 ቀበሌ እንዲሁም በዲረሙ እና በደንቢ ግራርጌ ቀበሌም እየተካሄደ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበክልሉ ያለውን የሰላም ችግር በውይይት ለመፍታት በፋርጣ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች የሰላም ኮንፈረንስ ተካሄደ፡፡
Next article“ከተረጅነት ወደ ምርታማነት” በሚል መልዕክት ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ልማት የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው።