የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ተጀመረ።

27

ባሕር ዳር: ሰኔ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና ግቢ በይፋ ተጀምሯል። የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሩን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሰሀ ይታገሱ(ዶ.ር) እና የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጁሀር አስጀምረዋል።

በመርሐ ግብሩ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሰሀ ይታገሱ(ዶ.ር) እና ከንቲባ ከድር ጁሀርን ጨምሮ የካቢኔ አባላት፣ የኮርፖሬሽኑ መሪዎች፣ የከተማው ወጣቶች እና ሴቶች፣ የፀጥታ አካላት፣ የነፃ ንግድ ቀጣናው ማኅበረሰብ እንዲሁም ሌሎች አካላት ተሳታፊ ኾነዋል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በመላው ሀገሪቱ በሚያስተዳድራቸው ግዙፍ የኢንቨስትመንት ማዕከላት በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ሀገር በቀል ችግኞች እንደሚተከሉ ከኮርፖሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ባለፉት ዓመታት በኢንዱስትሪ ፓርኮች በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሮች የተተከሉ ችግኞች ለምግብነት እና ለጥላነት የሚያገለግሉ ሲሆን የመፅደቅ ምጣኔያቸውም ከ85 በመቶ በላይ መሆኑ በመረጃው ተመላክቷል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።
Next articleበክልሉ ያለውን የሰላም ችግር በውይይት ለመፍታት በፋርጣ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች የሰላም ኮንፈረንስ ተካሄደ፡፡