ከተረጅነት ወደ አምራችነት ለመሸጋገር ያለመ ውይይት በሰቆጣ ከተማ እየተካሄደ ነው።

44

ባሕር ዳር: ሰኔ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በሰቆጣ ከተማ “ከተረጅነት ወደ ምርታማነት የተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነት” በሚል መሪ መልእክት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ዞናዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማሥተባበሪያ ተጠሪ ጽሕፈት ቤት የተዘጋጀው ይህ መድረክ ዋና ዓላማው ዋግ ኽምራን ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ማሸጋገር ነው። በውይይት መድረኩም የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ዋና አሥተዳዳሪን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ አሥፈጻሚዎች፣ የወረዳ መሪዎች፣ የወረዳ አደጋ መከላከል እና የምግብ ዋስትና ተጠሪ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል።

በውይይት መድረኩም ዞኑን ከተረጅነት በማላቀቅ ወደ አምራችነት እንዲሸጋገር የሚያደርጉ የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎች ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፦ ደጀን ታምሩ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የኦንላይን ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ የሚሠራጨው መረጃ ሐሰተኛ ነው” ትምህርት ሚኒስቴር
Next articleበማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።