“የኦንላይን ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ የሚሠራጨው መረጃ ሐሰተኛ ነው” ትምህርት ሚኒስቴር

26

ባሕር ዳር: ሰኔ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የኦንላይን ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ የሚሠራጨው መረጃም ፍጹም ከእውነት የራቀ ሐሰተኛ መኾኑን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡

በመሆኑም ተማሪዎች ፈተናው በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ ዐውቀው ዝግጅታቸውን እንዲቀጥሉ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢትዮጵያውያንን ለመታደግ የተዘጋጀው የሙዚቃ ድግሥ
Next articleከተረጅነት ወደ አምራችነት ለመሸጋገር ያለመ ውይይት በሰቆጣ ከተማ እየተካሄደ ነው።