“ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች እያሳካቻቸው ያሉትን ስኬቶች ለማስቀጠል፤ ሰላም በእጅጉ ያስፈልጋታል” አቶ ብናልፍ አንዱዓለም

27

ባሕር ዳር: ሰኔ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ስለ ሰላም ግንዛቤ በመፍጠር ዜጎች ለሰላም መረጋገጥ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ለማድረግ ያለመ የሰላም ሩጫ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች በመካሄድ ላይ ነው።
በአዲስ አበባም “ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ የሰላም ሩጫ ውድድር እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሐ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለምን ጨምሮ ሌሎች የፌደራል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ ታዋቂ አትሌቶች እና ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል።

በዚሁ ወቅት የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዱዓለም ኢትዮጵያ ከሁሉም በላይ ሰላም ያስፈልጋታል ብለዋል።
የሰላም ሩጫው ዋና አላማ የሰላም ፍላጎታችንን ከፍ አድርገን ለማሳየት ነው በማለት ጨምረው ገልጸዋል።
ሰላም የሁሉም መሰረት ነው ያሉት ሚኒስትሩ ፤ ሁላችንም ለሰላም በሰላም መተባበር አለብን ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች እያሳካቻቸው ያሉትን ስኬቶች ለማስቀጠል፤ ሰላም በእጅጉ ያስፈልጋታል ነው ያሉት።

እንደ ኢዜአ ዘገባ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለው ይህ የሰላም ሩጫ የተዘጋጀው በሰላም ሚኒስቴር እና በአጋር አካላት ትብብር ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የኢንዱስትሪ ሽግግሩን የሚያሳካ ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት ለቴክኒክ እና ሙያ ሥልጠና ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል” ሙፈሪሃት ካሚል
Next articleኢትዮጵያውያንን ለመታደግ የተዘጋጀው የሙዚቃ ድግሥ