
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን ስማዳ ወረዳ ዉስጥ በሚገኙ ቀበሌዎች በወቅታዊ የሰላም እና ደኅንነት ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክር ሕዝባዊ ዉይይቶች ተካሂደዋል።
በዉይይቱ ላይ በክልልም ሆነ በአካባቢ ደረጃ ከተጋረጠብን የፀጥታ ችግር እንዴት እንዉጣ እና ለሰላም ማስፈን ሥራችን ማኅበረሰቡን ጨምሮ በየደረጃዉ ካለዉ የማኅበረሰብ ክፍል ምን ይጠበቃል? በሚሉ አርዕስተ ጉዳዮች ዙሪያ እንደመከረ ተገልጿል።
ክልላችንና አካባቢያችንን ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሲቪክ ማኅበራት ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚጠበቅባቸዉ የገለፁት የወረዳው ነዋሪዎቹ በአካባቢያችንና በክልላችን የገጠመውን የሰላም እጦት ችግር ለመፍታት የተቋቋመውን የሰላም ካውንስል ሁሉም ማኅበረሰብ ሊደግፈው እንደሚገባም አሳስበዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!