
ባሕር ዳር: ሰኔ 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በደሴ ከተማ አሥተዳደር በ26ቱም ቀበሌዎች “ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት ሕዝባዊ የሰላም ኮንፈረንስ ተካሂዷል።
የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች የሰላም መስፈን ጥቅሙ ለሁላችንም ነው ብለዋል። የሰላም ማጣት ደግሞ በተመሳሳይ መልኩ ሁላችንንም የሚጎዳ በመኾኑ የሕግ የበላይነት መከበር እና የሰላም መስፈን ጉዳይ ለሁሉም ዜጋ ወሳኝ መኾኑን ተናግረዋል።
በሃሳብ የበላይነት በማመን እና ተባብሮ በመሥራት የሰላም እንቅፋቶችን ማስወገድ ለነገ የማይባል የሁሉም ዜጋ ድርሻ ሊኾን እንደሚገባም ተናግረዋል።
ብዝኀነትን ያከበረ ዴሞክራሲያዊ አብሮነት እንዲጎለብት አንድነትን የሚፈትኑ ኃይሎች ሰላማዊ የትግል ስልትን እንዲከተሉ ማድረግ የሁሉም ኅብረተሰብ ክፍል ኀላፊነት እንደኾነም በውይይቱ ተመላክቷል።
የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነቶች ቢኖሩም በሀገራዊ ልማት፣ ዘላቂ ሰላም እና አንድነትን ጉዳይ ላይ መደራደር እንደማይገባ በውይይቱ ተነስቷል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!