የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ5 ሺህ 900 በላይ ተማሪዎቹን አስመረቀ።

23

አዲስ አበባ: ሰኔ 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ)አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ5 ሺህ 900 በላይ ተማሪዎቹን ለ74ኛ ጊዜ በሚሊኒየም አዳራሽ አስመርቋል።

ዩኒቨርስቲው ዛሬ ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል 51 በመቶ የሚኾኑት የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ሲኾኑ ከመጀመሪ ዲግሪ ተመራቂዎች መካከል ደግሞ 36 ከመቶ ሴቶች ናቸው ተብሏል።

በምረቃ ሥነ ስርዓቱ የዩኒቨርሲቲው ቻንስለር እና የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ ፍሬሕይዎት ታምሩ፣ የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚደንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ እና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች፣ የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የዛሬ ተመራቂዎች ከኛ የተሻለ ጊዜ ላይ ያላችሁ በመኾናችሁ ኢትዮጵያ ከናንተ ብዙ ትጠብቃለች ብለዋል።

ጥቂት ጊዜ ቢኾንም በዩኒቨርሲቲው የቀሰማችሁት ጥራት ያለው እና የተሻሻለ የትምህርት አሰጣጥ ሥርዓት በሥራ ዓለም የተሻለ እውቀት እና ሥነ ምግባር ይዛችሁ እንድትወጡ የሚያግዝ ነው ብለዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ተመራቂዎች በምትሰማሩበት የሙያ መስክ በኀላፊነት መሥራት እና የተሻለ አስተዋፅኦ ማበርከት ይገባችኋል ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ.ር) በበኩላው ዩኒቨርሲቲው ራስገዝ ከኾነ በኋላ የተመረቃችሁ የመጀመሪያዎቹ ተማሪዎች በመኾናችሁ ታሪካዊ የዩኒቨርሲቲው ተመራቂዎች ያደርጋችኋል ብለዋል።

ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ዩኒቨርሲቲው ራስገዝ አስተዳደር ኾኖ ፍሬያማ እና ኢትዮጵያን የሚያሻግር ትውልድ ለመፍጠር በርካታ የለውጥ ሥራዎችን እያከናወነ ነው ብለዋል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው የምረቃ መርሐ ግብር በአጠቃላይ ከ5 ሺህ 900 በላይ ተማሪዎችን አሰረመርቋል።

ዘጋቢ፦ ድልነሳ መንግሥቴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የብዙ ምንጮች መፍለቂያ፣ የድንቅ ተፈጥሮ መገኛ፣ የእምቅ የቱሪዝም ባለቤት፣ የሀገር ሽማግሌዎች ምድር አርባ ምንጭ!” ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ
Next article“ግጭቱ ይበቃል ወደ ሰላም ተመለሱ ችግሩ ከአቅማችን በላይ ሁኗል” የደሴ ዙሪያ ወረዳ አርሶ አደሮች